በመቅደላ ጦርነት ምክንያት የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶች አሁንም ከየአካባቢው ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡
አለም አቀፉ ዘ-አርት ጋዜጣ ከሰሞኑ ባስነበበው የምርመራ ስራው ከ 500 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው ባለ ቀለም ቅብ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ከአጼ ቴዎድሮስ መኝታ ራስጌ ላይ ከተሰቀለበት ኤፕሪል 13፣ 1868 ተዘርፈው ከተወሰዱ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ፋይዳ ከነበራቸው ምስሎች አንዱና ውዱ እንደሆነ ጋዜጣው ገልጿል፡፡
ከመቅደላ ጦርነት በኋላ ጥንታዊ ቅርሶችንና ጽሁፎችን ከኢትዮጵያ እንዲያመጣ የተላከውና የብሪትሽ ሙዚየም መልዕክተኛ የነበረው ሪቻርድ ሆምስ ይህን ውብ ባለቀለም ምስል በወቅቱ ወደ ብሪታኒያ ቢያመጣም በወቅቱ ለሙዚየሙ አለማስረከቡን ጋዜጣው በምርመራ ዘገባው ላይ አስፍሯል፡፡
ግለሰቡ ይህን ምስል ክርሰቲ ለተባለ ስነጥበብ ተኮር ለሆኑ ጥንታዊና ዘመናዊ ቅርሶች አጫራች ለሆነው የንግድ ድርጅት በማቅረብ እ.ኤ.አ. በ 1917 መሸጡን ጋዜጣው አስነብቧል፡፡
Kwer’ata Re’esu በመባል የሚታወቀው ባለቀለም ቅብ ምስል ከፊት ለፊቱና ከኋላው የግዕዝ ጽሁፍ ያለበት ሲሆን የኢትዮጵያ ነገስታት እሰከ 1868 ድረስ እየተቀባበሉት መቆየታቸውን አመልክቷል፡፡ ባለቤትነቱ ከኢትዮጵያ እንዳይመስል በርካታ ጥረቶች መደረጋቸውንና ስሙንም በወቅቱ ከኢትዮጵያ በሚል የማንሳት ፍላጎት እንዳልነበረ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ነገስታቶች ወደ ጦር ሜዳ ሲሄዱ ከዚህ ምስል ፊት ቆመው ጸሎት ያደርጉ እንደነበር ጋዜጣው ይገልጻል፡፡
በርካታ ጦርነቶችን እና የእሳት ቃጠሎዎችን በማለፉ በየዘመኑ ተአምራዊ ተደርጎ ይታይ የነበረው ይህ ምስል ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥሪ ማቅረብ ይገባል ያለው ጋዜጠኛ ምስሉ በጥቂት ሰዎች ብቻ የታየ በመሆኑ ትኩረት ውስጥ ሳይገባ ሊቆይ እንደቻለ አክሎ ገልጿል፡፡
ምስሉ ከባለቤቶቹና ከጥቂት ሰዎች በስተቀር እስከ አሁን በማንም እንዳልታየ ያመለከተው ጋዜጣው ይህ ምስል በፖርቹጋል የውድ ሀብቶች ማስቀመጫ ባንክ ውስጥ እንደሚገኝ በምርመራው እንደ ደረሰበት አስታውቋል፡፡
ለዘመናት ከስፍራ ስፍራ እና ከባለቤት ባለቤት እንደመዞሩ ሳይሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምስሉ እንዲመለስ ከፖርቹጋል መንግስት ጋር ንግግር መጀመር ያስፈልጋል በማለት አስተያየቱን ገልጿል፡፡
የፖርቹጋል መንግስት ይህ ምስል ከመንግስት ፍቃድ ውጪ ከሀገሩ እንዳይወጣ እ.ኤ.አ. በ 2002 ባወጣው መመሪያ መደንገጉም ታውቋል፡፡
ከሰሞኑ ከብሪታኒያ እየተመለሱ ያሉ ቅርሶች ለዚህ ምርመራ መነሳሳት ምክንያት እንደሆነ ጋዜጣው አመላክቷል፡፡
Via: theartnewspaper
Latest News
Browse allwe appreciate your help.