በኢትዮጵያዊ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ለንደን
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ዳር ድንበር በማስከበርና ለትግራይ ህዝብ ደህንነት፣ ደጀንና ዋስትና በመሆን ላለፉት 20 ዓመታት በየጊዜው ሲሰነዘር የነበረ ጥቃትን በመመከት የህይወት መስዋዕትነት ሲከፍል ኖሯል፡፡
ነገር ግን ሕወሓት በትናንትናው እለት ትግራይ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመፈፀም ዝርፊያ ለማድረግ ሞክሯል፡፡
ይህን ታሪካዊ የክህደት ተግባር ተከትሎ የፌዴራል መንግስት ሕወሓት የፈፀመውን እኩይ ድርጊትና የሀገር ሉአላዊነትን አደጋ ላይ የጣለ አሳፋሪ ተግባር መቀልበስና ማምከን የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤትም አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ እና በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሚመራ ግብረሐይል በማቋቋም ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልል ላይ አውጇል፡፡
በመሆኑም በዩናይትድ ኪንግደምና ሰሜን አየርላንድ የምትገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሁኔታውን በስክነትና በማስተዋል እንድትከታተሉና የሀገራችንን ህልውና እና የሕዝባችንን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረግ ኢትዮጵያን የማዳን እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በመገንዘብ ከመንግስት ጐን እንድትቆሙ እንዲሁም የሀገራችንን አንድነት ለማረጋገጥ እና ህብረ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ የፌዴራል ሥርዓት ለማጠናከር የተጀመረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ኤምባሲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
Latest News
Browse allwe appreciate your help.