Duty-Free Notes

ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ።

  • አገልግሎቱን ለመጠየቅ አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል።

  • በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም።

አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ

1)

በኤምባሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ መሙላት

2)

ወደ ሀገር የሚያስገቧቸውን የግል መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር ማቅረብ

3)

የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመበት “Commercial Invoice” ማቅረብ

4)

የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመው ከዩኬ ውጪ ከሆነ፣ ግዢው በተፈፀመበት ሀገር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚሲዮን Commercial Invoice መረጋገጥ ይኖርበታል

5)

የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ ፓስፖርት ዋናው እና ኮፒ ወይም

6)

ፓስፖርት የሌላቸው ደግሞ ከኤምባሲ የተሰጠ የይለፍ ወረቀት/ሊሴፓሴ
     7) የብሪቲሽ መኖሪያ ፈቃድ /Resident permit or ID/ መሰረዙን የሚያረጋግጥ ሰነድ/ማስረጃ
  ማስታወሻ ፡- ከላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች ተሟልተው ሲቀርቡ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X