ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ በግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 51/2010 መሰረት እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች
- እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡
- አገልግሎቱን ለመጠየቅ አንድ አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል።
- በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም፡፡
- የግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 51/2010፣ ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡ፣ የግል መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር (PDF)
አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ
በልዩ ልዩ ምክንያት ውጭ ሀገር ቆይተው ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን
ለንግድ ዓላማ የማይውል የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲሁም የቤት መኪና ቀረጥ ከፍለው ማስገባት እንዲችሉ መሟላት ያለባቸው፡-
1. በኤምባሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ መሙላት
2. ወደ ሀገር የሚያስገቧቸውን የግል መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር ማቅረብ
3. የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመበት “Commercial Invoice” ማቅረብ
4. የቤት አውቶሞቢል/መኪና ግዢ የተፈጸመው ከዩኬ ውጪ ከሆነ፣ግዢው በተፈፀመበት ሀገር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚሲዮን Commercial Invoice መረጋገጥ ይኖርበታል
5. የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ ፓስፖርት ዋናው እና ኮፒ ወይም
6. ፓስፖርት የሌላቸው ደግሞ ከኤምባሲ የተሰጠ የይለፍ ወረቀት/ሊሴፓሴ
7. የብሪቲሽ መኖሪያ ፈቃድ /Resident permit or ID/ መሰረዙን የሚያረጋግጥ ሰነድ/ማስረጃ
ማስታወሻ ፡- ከላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች ተሟልተው ሲቀርቡ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል።
- Essential GRED Bond information as presented by the Commercial Bank of Ethiopia – PDF
- CBE BOND Forms – PDF
Ethiopians and Foreign Nationals of Ethiopian origin living and working outside Ethiopia are eligible to open a Diaspora Bank Account with the Commercial Bank of Ethiopia.
You can open a Diaspora Account in 3 easy steps. For further information on the types of accounts available, please visit the Commercial Bank of Ethiopia website.
- Complete Application Form – PDF
- Gather Supporting Documents
- Completed application form
- Your passport
- One recent passport-sized photo