ለቆንስላ አገልግሎት ጠያቂዎች
በለንደን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ የፓስፖርት እና የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎቶች በከፊል በኤምባሲው ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
እነዚህ አገልግሎቶች በተሟላ ሁኔታ በኤምባሲው ለመስጠት አዲስ ሥርዓት የመዘርጋት አሰራር የተጠናቀቀ መሆኑን በመግለጽ አገልግሎቱ በኤምባሲው እንደሚጀመር ማሳወቃችን ይታወሳል።
በዚሁ መሰረት የፓስፖርት እድሳት አገልግሎ ከመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 5 ቀን 2026) ጀምሮ በለንደን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ መጀመሩን በደስታ እያሳወቅን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እና የአዲስ ፓስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ በቅርብ ስራ ስንጀምር የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን የተጀመሩ የኦንላይን አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚከተለውን ድረ-ገጽ እንድትጠቀሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።
To Applicants for Consular Services at the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in London
The Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in London has been providing, on a limited basis, passport and Ethiopian-origin identification card services at the Embassy.
The Embassy is pleased to announce that the establishment of a new system for the full provision of these consular services at the Embassy has now been completed.
Accordingly, the Embassy has the honour to inform members of the public that, effective 5 October 2026, passport renewal services have commenced at the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in London. Ethiopian Origin Identification Card and new passport application services will be announced separately once they commence.
Applicants wishing to obtain these services are respectfully requested to use the website indicated below for further information and access to the relevant services.