በለንደን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ ሪፐብሊክ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ የበይነ መረብ ውይይት አደረገ።
በውይይቱ ወቅት ወደ 100 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እና ቀጣይ የልማት አቅጣጫዎች እንዲሁም ወቅታዊ ተግዳሮቶች ተዳሰዋል::
ተሳታፊዎቹ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት ያላቸውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ፣ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት በመተባበር ለሀገራዊ ልማት የበኩላቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

